ከውጪ የሚመጡ ምርቶች

ሶላር

ሶላር ቴክኖሎጂ የታዳሽ ኃይል ስርዓት ለንግድ ሴክተሩ በአሠራሩ፣ በአተካከሉና ለጥገና ምቹነቱ ወደር የሌለው ነው፡፡

የብርሃን ምንጭ ሀይል ማከማቻ መሳሪያ (ባትሪ) አይነተኛ አገልግሎቶች፤

ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲሁም ሌሎች የመገልገያ መሳርያዎችን ቻርጅ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ፤

  • ባለ ሶስት ቀለም ብርሃን አምፑሎች ያሉትና ርዝማኔው 3ሜትር የሆነ ኬብል እንዲኖረው ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑ፤
  • የአምፖሎቹ ብርሃን ዓይንን እንዳያውክ ነጭ የመከላከያ ሽፋን እንዲኖረው ሆኖ መዘጋጀቱ፤
  • የኃይል ጣቢያዉ ከኤሌክተሪክ መስመር ጋር ግኑኝነት በሌላቸው አስቸጋሪ ቦታዎች፤ ተራራዎች፣ መጋዘኖች የተመረጠ የመብራት ምንጭ ነው፡፡ እያንዳንዱ አምፑል 9 ካሜ ስፋት ላለው ክፍል በቂ ብርሃን ይሰጣል፡

ሊፍት/አሳንስር/

ሊፍቶቹ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውና ለንግድ ማዕከላት፤ለመኖርያ ቤቶች፤ ለሆቴሎች፤ለምግብ አዳራሽና ለቢሮ ህንጻዎች እንዲሁም ለኤርፖርቶች አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ናቸው፡፡

የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች

በሀገራችን በሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎቻችን ተደራሽና መሰረታዊ የጤና አገልግሎት በማግኘት ላይ እንዳልሆኑ ይታወቃል በሺዎች የሚቆጠሩ የበሽታ መንስኤዎች ተገቢው ህክምና እተደረገላቸው አይደለም በርካቶች በተለያየ በሽታ እየተጠቁ ናቸው፤ በመሆኑም ቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር ይህን ሀገራዊ የጤና ችግር አስመልክቶ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት የድርሻውን እያበረከተ ይገኛል፡፡ድርጅታችን የተለያዩ አገልግሎቶችን በማቅረብ ይታወቃል ይህም ብቻ ሳይሆን ፤የምክር አገልግሎት በመስተት፤የአቅርቦቱን ዝርዝር ለደምበኞች በማቅረብ፣ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን እና ጅምላ ሽያጭ ስራ ላይ የተሰማራ ከመሆኑም በላይ ከዘላቂ ንግድ ስራዎች ጋር በተያያዘም ለተጠቃሚዎቻችን የጤና መጠበቂያ ምርቶችን በማቅረብና የክፍያ ድርሻችንን በማሳደግ ሰፊውን የህብረተሰባችንን ክፍል እንደግፋለን፡፡

ተርማል ወረቀት

የጽህፈት መሳርያዎች አቅርቦት(stationary)ሲሆን ከፍተኛ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ፡- በሁለት ፊት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ለፎቶ ኮፒ ለህትመት ስራ ተመራጭና በጄት የህትመት ቀለም ላሰር ለመጠቀም የሚያስችሉ ወረቀቶች ናቸው፡፡.ይህም ብቻ ሳይሆን ለከለር ህትመት አገልግሎት ለካሽ ሬጂስተር ማሽኖች አገልግሎት የሚውልና በሙቀት እንዳይበላሽ እንዲሁም ክብደት እንዳይኖረው ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ለህንጻ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው/ፌሮ/ የብረት ዘንጎች

ወደ ሀገር ውስጥ ከምናስገባቸው ምርቶች አንዱ ለተለያዩ የህንጻ አካል ግንባታ የሚውሉ ፌሮዎች ሲሆኑ ከነዚህም ዋነኛው ግሬድ 60 የተባለው ነው ይህም የግንባታ ብረት የሚሰጠው የመሸከም አቅም 60.000 ፓውንድ/ ሰኩየር ነው፡፡ ይህም በዘመናዊው የሜትሪክ ልኬት 420 ሜጋ/ፒክስል ይሆናል፡፡ይህም ብቻ ሳይሆን ማጠናከርያ ብረቱ በዙርያው ከፍተኛ የድጋፍ አቅም የሚፈጥር ሲሆን ይህም አምስት ዕጅ የሚሰፋ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ግሬድ 60 በመባል የሚታወቀው የማጠናከርያ ብረት ለከፍተኛና መካከለኛ ህንጻዎች ግንባታ ተመራጭ እንደሆነ ይታወቃል