የሁመራ ሰሊጥ ዝርያ

Product Category: 
Seasame

የሁመራ ሰሊጥ ዝርያ በርካታ ተመራጭ የሚያደርጉት ባህርያት ሲኖሩት ከነኝህም ዋነኛው በማሽን ንጽህናው የተጠበቀው ምርት ጥራት 99 ከመቶ ሲሆን የባእድ አካላት መጠን እጅግ አነስተኛ እና 1ከመቶ ብቻ ነው፡፡ከዚህም ባሻገር (ከፍተኛው የቅባት አሲድ) ይዘት 1.5 ከመቶ ሲሆን የምግብ ዘይት ይዘቱ ዝቅተኛው 51 ከመቶ እንደሚሆን ይነገራል፡፡ በተያያዘም ከፍተኛ የርጥበት መጠን 7 ከመቶ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን በሀገር ውስጥ የደረጃ ምዘና እንደተረጋገጠው የተባይ ማስወገጃ የተደረገለት የሰሊጥ እህል በህይወት ካሉና ከሞቱ በራሪ ተባዮች ፍጹም የጸዳ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡