ስለ ቢሮው

በሌላ መልኩ ሌላኛው የክልሉ አርሶአደር ችግር የነበረው የተለያዩ የምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ችግርን ለማቃለል ጸረ ተባያና ጸረ አረም መድኃኒት፣ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በማቅረብ በተጫለው መጠን ወደ ሕዝብ በመቅረብ አገልግሎቱን የበለጠ በማጠናከር ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን የንግድ ሥራውን ይበልጥ በማጎልበትና በማስፋፋት በተለያዩ የኢምፖርትና ኤክስፖርት ሥራዎች ውስጥ ገብቷል፡፡ ከአመሰራረቱ በጫት የተጀመረዉ የንግድ ሥራ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያ እንዲሁም የእንስሳት መድሃኒት እና መገልጌ መሳሪያ አቅርቦትና ሽያጭ፤የፓልም የምግብ ዘይትአቅርቦትና ሽያጭ፣የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎች አቅርቦት ሽያጭ ጥገናና ሰርቪስ፣ ለሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎች አገልግሎት የሚዉል ተርማል ወረቀት አቅርቦትና ሽያጭ፣ የአርማታ ብረት አቅርቦትና ሽያጭ፤ የተለያዩ የሶላር መብራቶች አቅርቦትና ሽያጭ፤ አሳንሰር (ሊፍት)፣ የጎማ ግዢና ሽያጭ፣ የቅባት እህሎች፣ ቡናና ጫትን ኤክስፖርት በማድረግ እና የቢፍቱ ሕንጻን በመገንባት ለተጠቃሚዉ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ የደረሰበትን የንግድ እንቅስቃሴ እየሰፋ መሄዱን አመላካች ነዉ፡፡በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት ሥራዎች በ2008/2009 በጀት ዓመትም በዕቅድ ተይዘው ድርጅቱን ወደ ላቀ እድገት እንዲመሩ በትኩረት ይሰራል፡፡

ቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ መርሆዎች እና እሴቶች

ራዕይ

ተልዕኮ

እሴቶቻችን

ቢፍቱ አዱኛን በአገር ደራጃ በንግዱና በኢንቬስትሜንቱ ዘርፍ መሪ ሚና የሚጫወት ካምፓኒ ሆኖ ማየት ነው፡፡

የምናገለግለውን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ሊያጎለብቱ የሚችሉ፤ ምርትና ምርታማነት ሊጨምሩ የሚያስችሉ የገቢና ወጪ ንግዶችንና ኢንቬስትሜንት ስራዎችን፤ በሰራተኞቻችን እና በባላድርሻ አካላት ሙሉ ተሳትፎ፤ የእውቀትና ቴክኖሎጅ ድጋፍ በተከለበት ሁኔታ በማከናወን የክልሉንም ሆነ የአገራችንን የኢኮኖሚ እድገት ማሳደግ ነው፡፡

  • ሙስናን እንጸየፋለን፣
  • ተጠያቂነትን እናጎለብታለን፣
  • ውጤታማነት እናስገኛለን ፣
  • ግልጽነትን እናዳብራለን፣
  • ትርፋማነት መለያችን ነው፣
  • ወጪቆጣቢነት ምግባራችን ነው
  • በማያቌርጥ መሻሻል እናምናለን
  • ለጥራትና ለመልካም አገልግሎት በቁርጠኝነት እንሰራለን
  • ቲምወርክን እናጎለብታለን