ጂ3. የሶላር ሃይል አመንጪ መሳርያዎች

Product Category: 
Solar Technology

የተለያዩ የመጠን፣ የአይነትና የብዛት ልዩነት (Range) ያላቸው የሶላር ምርቶች እንደ ሶላር ላተርን ፣ ሶላር ቲቪ፣ ሶላር ሆም ሲስተም፣ ሶላር ጀኔሬተሮች፣ ሶላር ማቀዝቀዣ፣ ሶላር ቲቪ እና ሌሎችንም እናቀርባለን፡፡ ምርቶቹን እንሸጣለን፣ስለአጠቃቀሙም ለደንበኞቻችን ስልጠና እንሰጣለን፣ ድህረ ሽያጭ አገለግሎቶችንም እንሰጣለን፡፡

የንግድ ማዕከላችን የተለያየ ፍሪኩዌንሲ/ሞገድ/ ያላቸውን ሬድዮኖች አና ባለ5 ዋት የጸሀይ ብርሃን ሃይል ተጠቃሚ የአገልግሎት መቆጣጠርያ ስሪቶች/ፓነሎችን/ ያቀርባል፡፡

የመሣሪያው ዋና መለያ (Main Features)

 • አንዴ ኃይል ከተሞላ አስከ ሃያ ሰአታት ብርሃን ይሰጣል፡፡
 • የብርሀን መጨመሪያና መቀነሻ ሞድ ያለው ነው፡፡
 • የብርሃን ሰጪው አምፖል ለአጠቃቀም እንዲያመች በወለል እና/ወይም በጣራ ገበር (ኮርኒስ ላይ) ማንጠልጠያ ኖሮት የተዘጋጀ መሆኑ፤
 • መስቀያ ወይም ማንጥልጠያ የተሠራለት/ የተዘጋጀለት መሆኑ፤
 • የተንቀሳቃሽ ስልክ ቻርጅ ለማድረግ የሚያስችል ኬብል እንዲኖረው ሆኖ መዘጋጀቱ፤
 • በዘመናዊነታቸው የታወቁ /ስማርት/ ተንቀሳቃሽ ሞባይሎችን ቻርጅ ለማድረግ የሚችል ሆኖ መዘጋጀቱ፤
 • የሃይል ሰጪ ክፍሉን /ባትሪ/ የአገልግሎት ጊዜ ቀድሞ ለመረዳት የሚያስችል ንኡስ አካል እንዲኖረው ሆኖ መፈብረኩ፤
 • የኤፍ.ኤም.መቀበያ ሬዲዮኖች ከሞባይል ስልኮች ላይ በጆሮ ለማዳመጥ የሚያስችል አክሴሰሪ (መጠቀሚያ) እንዲሁም የድምጽ ማጉያዎች መለዋወጫዎች ማቅረብ መቻሉ፡፡
 • የፓነሎቹ የጀረባ አካል የተለያዩ ኬብሎችን ለመቀበል የሚያስችል ተቀባ የሶኬት ቀዳዳ እንዲኖረው ሆኖ የተዘጋጀ መሆኑ፤

የጂ3 የኃይል ማመንጫ መብራት

 1. ሞባይልን ቻርጅ ያደርጋል /በአንድ ጊዜ አንድ ሞባይል ቻርጅ ያደርጋል፡፡
 2. የተለያዩ ኤኤም እና ኤፍ ኤም ሬድዮኖችን ለማዳመጥ ያስችላል፡፡
 3. 5 ዋት ያለው የሶላር ኃይል መሰብሰቢያ ፓኔል አለው፡፡
 4. 120 ሉሜን ስታንዳርድ ያላቸው የብርሃን ሃይል የሚሰጡ የተለያየ ሞዴል አምፖሎች እንዲሁም ስማርት ተንቀሳቃሽ ስልክ ቻረጀር አለው፡፡ ሞዴል አር.ኤን.ጂ3 -5ዋት ባትሪ ›3.7 ቮልት ሃይል ይህም 3600 ሚሊ.አምፐር የኤሌክትሪከ ሃይል በሰአት የሚያመነጭ እና 120 ሉመን የብርሃን ጥንካሬ ያለው አምፖል ኖሮት እንደ አስፈላጊነቱ ከዋናው አካል ሊላቀቅ የሚችል ነው፡፡