×

Error message

  • Warning: mysqli_connect(): (HY000/1045): Access denied for user 'biftuadu'@'localhost' (using password: YES) in eval() (line 5 of /home2/biftuadu/public_html/am/modules/php/php.module(80) : eval()'d code).
  • Warning: mysqli_query() expects parameter 1 to be mysqli, boolean given in eval() (line 7 of /home2/biftuadu/public_html/am/modules/php/php.module(80) : eval()'d code).
  • Warning: mysqli_fetch_array() expects parameter 1 to be mysqli_result, null given in eval() (line 8 of /home2/biftuadu/public_html/am/modules/php/php.module(80) : eval()'d code).

በጥቂቱ ስለኛ

ቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አ.ማ. የምስራቅ እና ምዕራብ ሃረርጌ አርሶአደርን የጫት ምርት ተጠቃሚነት ችግርን ለመፍታት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ለሁለት አስርተ ተከታታይ ዓመታት በላይ በጫት ኤክስፖርት ሥራ ላይ የተሰማራና ይህንኑ ምርት ወደ ጎረቤት ሀገሮች ጅቡቲና ሱማሊያ በመላክ የገበሬውን ችግር ለመፍተግባር ላይ ያለ የህዝብ ድርጅት ነው፡፡

በሌላ መልኩ ሌላኛው የክልሉ አርሶአደር  ችግር የነበረው የተለያዩ የምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ችግርን ለማቃለል ጸረ ተባያና ጸረ አረም መድኃኒት፣ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በማቅረብ በተጫለው መጠን ወደ ሕዝብ በመቅረብ አገልግሎቱን የበለጠ በማጠናከር ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን የንግድ ሥራውን ይበልጥ በማጎልበትና በማስፋፋት በተለያዩ የኢምፖርትና ኤክስፖርት ሥራዎች ውስጥ ገብቷል፡፡
ከአመሰራረቱ በጫት የተጀመረዉ የንግድ ሥራ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያ እንዲሁም የእንስሳት መድሃኒት እና መገልጌ መሳሪያ አቅርቦትና ሽያጭ፤የፓልም የምግብ ዘይትአቅርቦትና ሽያጭ፣የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎች አቅርቦት ሽያጭ ጥገናና ሰርቪስ፣ ለሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎች አገልግሎት የሚዉል ተርማል ወረቀት አቅርቦትና ሽያጭ፣ የአርማታ ብረት አቅርቦትና ሽያጭ፤ የተለያዩ የሶላር መብራቶች አቅርቦትና ሽያጭ፤ አሳንሰር (ሊፍት)፣ የጎማ ግዢና ሽያጭ፣ የቅባት እህሎች፣ ቡናና ጫትን ኤክስፖርት በማድረግ እና የቢፍቱ ሕንጻን በመገንባት ለተጠቃሚዉ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ የደረሰበትን የንግድ እንቅስቃሴ እየሰፋ መሄዱን አመላካች ነዉ፡፡በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት ሥራዎች በ2008/2009 በጀት ዓመትም በዕቅድ ተይዘው ድርጅቱን ወደ ላቀ እድገት እንዲመሩ በትኩረት ይሰራል፡፡
በተጨማሪም በዚሁ በጀት ዓመት በመንግሥት በጥናት ታቅፈዉ ወደ ተግባር ይገባሉ ተብለዉ የተያዙ ሥራዎች እንዲሁም ከሽያጭ ማዕከሎቻችን ተጠንተዉ የሚቀርቡ የተለያዩ ምርቶች አዋጭነታቸዉ ተረጋግጦ ወደ ትግበራ የሚገቡ ይሆናሉ፡፡ ሴራሚክ፤ የመጸዳጃ ቤት ዕቃዎች፤ ጨርቃ ጨርቅ፤ የተለያየ መጠን ያላቸዉ ማስታወሻዎች፤ ሲሚንቶ፤ የአገር ዉስጥ ብረታ ብረት፤ ኦሞ፤ የተለያዩ ሳሙናዎች፤ ዱቄት፤ ማቀዝቀዣ፤ ፕሪንተር በጥናት ላይ ተመስርቶ ሥራ ላይ እንዲዉሉ ይደረጋል፡፡
በመሆኑም ድርጅቱ በየዓመቱ በዕቅድ እየያዘ ከሚያከናዉናቸዉ የወጪና የገቢ የንግድ ሥራዎች ልምድ እያካበተና ይህንኑን ልምድ በመጠቀም ሰፋ ወዳለ የንግድ እና የኮሚሽን ሥራዎች ዉስጥ ለመግባት የሚያስችለዉ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሎ ማየት ይቻላል፡፡ 
ይህ በእንዲህ እያለ ድርጅቱ ሲጠቀምበት የነበረዉ ነባሩ ድርጅታዊ መዋቅር እየሰፋ ከሚሄደዉ ሥራ ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ አዲስ ድርጅታዊ መዋቅር በማስጠናትና ሥራ ላይ በማዋል በሰባት ዳሬክቶሬቶች እና በሕንጻ አስተዳደር ተደራጅቶ በሰዉ ኃይል፤በበጀትና በሎጅስቲክ ተጠናክሮ የ2008 /2009 በጀት ዓመት ዕቅዱን ለማስፈጸም ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ስለዚህ በ2007/08 በጀት ዓመት ድርጅቱ ከተሰማራባቸው የኢምፖርት፣ ኤክስፖርት እና የአገልግሎት ሽያጭ ከታክስ በፊት ያልተጣራ ትርፍ 86,858,308 ብር ትርፍ ለማግኘት ፡፡ የዕቅድ አፈጻጸሙም ያልተጣራ ትርፍ ከታክስ በፊት 90,334,995.75  ብር ሲሆን በመቶኛ ሲሰላ 104 በመቶ  ነው፡፡ ይህም ማለት በበጀት ዓመቱ ከታቀደው 60,800,815.60 የተጣራ የትርፍ መጠን  በብር 2,433,681.43 የሚበልጥ የተጣራ ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን ያሳያል፡፡

የ2008/2009 በጀት ዓመትን ዕቅድ ለማዘጋጀትና ተግባራዊ ለማድረግ የ2007/2008 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ በማድረግ እና በግምገማው ወቅት የተለዩትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም የነበሩ ስጋቶችና መልካም እድሎች ለበጀት አመቱ ዕቅድ ዝግጅት በግብአትነት እንዲወሰዱ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ድርጅቱ በአዲሱ ድርጅታዊ መዋቅር መሠረት ሽያጩንና ተደራሽነቱን የበለጠ ለማስፋት በጥናት ላይ ተመስርቶ አዳዲስ የሽያጭ ማዕከሎች እንዲከፈቱ የሚያደርግ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱም ብቃትና ጥራት ያለው የሰዉ ኃይል በቅጥር እንዲሟላ ይደረጋል፡፡  የነባር ሠራተኞችንም የሙያ ክፍተት በመለየት የተለያየ የሙያ ላይ ስልጠና የሚሰጣቸዉ ይሆናል፡፡

ስለሆነም በ2008/2009 በጀት ዓመት ከሀገር ውስጥ ሽያጭ  116,103,114.17 ብር፣ ከኤክስፖርት ዘርፍ 14,036,904.73፣ ከአገልግሎት ዘርፍና ሌሎች 18,442,244.83 ያልተጣራ ትርፍ  እና ድርጅቱ በሌሎች ድርጅቶች ካደረጋቸው  ኢንቨስትመንቶች 1,652,494.33 ያልተጣራ ትርፍ በድምሩ ብር 150,234,758.06 ጠቅላላ ትርፍ  ይገኛል ተብሎ ታቅዷል፡፡

ከምርቶቻችን በጥቂቱ

የፀሐይ ቴክኖሎጂ

የተለያዩ የፀሃይ ምርቶችን እንደ ሶልትራቶን መብራት, የፀሃይ ስርዓት ቤት, የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች, የፀሐይ ማቀዝቀዣ, የፀሐይ ቴሌቪዥን እና ሌሎችንም ያቀርባል. ምርቱን እናሸጥነዋለን, ደንበኞችን በአጠቃቀም ላይ እናምናለን እና የሽያጭ አገልግሎቶችን እናቀርባለን

ገንዘብ መዝጋቢ ማሽኖች

የሽያጭ ቅርንጫፎች እና የተጫነ የሽያጭ እና የቴክኒክ ሠራተኞች በደንበኞቻችን እና በገቢ ባለስልጣን መካከል ግንኙነቶችን ለመፍጠር እኛን የሚያመላክት የጠንካራ ሽያጭ እና የአገልግሎት አውታረ መረቡ. ስርዓቱን በማስተዳደር ረገድ ሰፊ ልምድ አለን.

የሕክምና እና የመድኃኒት አቅርቦት

የማማከር, የምስጢር ዝግጅት, ማስመጣት እና ሙሉ ሽያጭን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንሰጣለን

አግሮ-ኬሚካሎች

በአገሪቱ ውስጥ የአግኖ-ኬሚካሎች ማስመጣትና ማከፋፈል በረጅም ጊዜ ልምድ አለን. ከአምራች ገበሬ ማህበራት እና ነጋዴዎች ጋር የግብርና ኬሚካሎችን በተለያዩ ገበሬዎች ለሚያቀርቡ ነጋዴዎች እንሰራለን

የብረት ውጤቶች እና ሬብ

የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ የግንባታ ኢንዱስትሪ እያደገ ነው. የግንባታ እንቅስቃሴዎችና በመሠረተ ልማቶች ላይ የተገነቡት የአረብ ብረት ምርቶች ከፍተኛ መሆን አለባቸው. የአረብ ብረት ምርቶችን በማስመጣት እና በማሰራጨት ላይ ንቁ ተሳታለን

ቡና

የተለያዩ የኢትዮጵያ ቡና ዓይነቶች ከሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ደንበኞች ጋር አብረን እንሰራለን. የቡና አረቢያ ቡና ዋናው የቡና ዓይነት ሲሆን ለደንበኛው ፍላጎት መሰረት የምንሰጠው የተለያዩ የምግብና ጣዕም አለ. በምሰጠው ምርት ጥራት እና ልቀት ላይ ልዩ ትኩረት እንሰጣለን

የጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች

ጥራጥሬዎችን እና የዘይት ዘርን ለአለም አቀፍ ገበያ እናቀርባለን. የኢትዮጵያ የዘር ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ይህንን ሚና እንጫወታለን

እህት ኩባንያ